Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland
By ECF in Finland
Ethiopian Christian Fellowship Church in FinlandSep 10, 2023
328 || ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል! || በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር)
"ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል!" በሚል ርዕስ በሉቃ.18፡18-26 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
327 || አስተዋይ እናት - ማሪያም || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
በእናቶች ቀን የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
አስተዋይ እናት - ማሪያም
ሉቃ. 1፡ ላይ የተመሠረተ
326 || የዘላለም ህይወት ቃል! || ወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"የዘላለም ህይወት ቃል!" በሚል ርዕስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መነሻ ክፍል፡ ዮሐ. 6፡68-69
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 6፡1-68፣ ዘፍ. 2፡7፣ ዮሐ. 1፡3-4፣ 1 ቆሮ. 2፡13-15፣ 2 ቆሮ. 4፡16-18፣ ዮሐ. 17፡3፣ ዘፍ. 3፡22-24፣ 1 ቆሮ. 1፡8
ይዘት
መግቢያ
1) ህይወት
2) የዘላለም ህይወት
3) የዘላለም ህይወት ቃል
ማጠቃለያ
325 || ለወደደን! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"በወደደን!" በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ 1፡5-6
324 || አብረኸኝ መከራን ተቀበል! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"አብረኸኝ መከራን ተቀበል!" በሚል ርዕስ በ2 ጢሞቴዎስ ላይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 2 ጢሞቴዎስ 1-4
ሀ) መግቢያ / ዮሐ. 16፡33፣ ሐዋ. 21፡1-14፣ ሐዋ. 9፡10-16፣ 2 ጢሞ. 1፡1-5
ለ) ሐዋሪያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን፣ "አብረኸኝ መከራን ተቀል!" ሲል ምን ማለቱ ነው?
1) በጌታችን ምስክርነት ወይም በእሥረኛው በእኔ አትፈር ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 1፡15-18፣ ሮሜ 1፡16
2) የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገርና የማያሳፍር ሠራተኛ ሁን ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 2፡15-19
3) በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እውነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከተል ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 2፡22፣ ምሳሌ 4፡23፣ ሉቃ. 6፡45
4) በተማርኽበትና በተረዳህበት ጸንተህ ቁም ማለቱ ነው። 2 ጢሞ.
5) አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 4፡5
323 || ምሥጋውን አትርሳ/ሺ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"ምሥጋናውን አትርሳሺ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ መዝ. 103፡1-6
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘዳ. 8፡1-20፣ መዝ. 106፡1-13፣ 1 ሳሙ. 7፡1-24
322b || የጦር ዕቃችን - የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ! || ወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ አጭር መልዕክት
በማስታወቂያ ክፍለ ጊዜ በወንድም ያቬሎ የተነበበ አጭር መልዕክት ከኤፌሶን መልዕክት 6፡10-18
322 || አምላካዊ መልስ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ
"አምላካዊ መልስ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 11፡1-6፣ 1 ነገ. 19፡1-18
መግቢያ
አምላካዊ መልስ የመጣላቸው 3 ሰዎች
- ኤልያስ፡ 1 ነገ. 19፡1-18
ሀ) የኤልያስ ክስ ዝርዝር (1 ነገ. 19፡10 እና 14)
- እስራኤላዊያን ቃል ኪዳንህን ትተዋል
- መሰዊያህን አፍርሰዋል
- ነቢያቶችህን ገድለዋል
- ብቻዬን አስቀርተውኛል
- እኔንም መግደል ይፈልጋሉ
ለ) አምላካዊ መልስ ሲመጣ ምን ሆነ? (1 ነገ. 19፡15-18)
- ኤልያስ ምሪት ወይም አቅጣጫ ተሰጠው/ምሪት አገኘ
- ሦስት ሰዎችን እንዲቀባ እግዚአብሔር ተናገረው
- ቅሬታዎች መኖራቸውን እግዚአብሄር ገለጠ
- ሙሴ፡ ዘጸ. 14፡10-18
ሀ) የህዝቡ ዕይታ/ 14፡10-12
ለ) የሙሴ ምላሽ/ 14፡13-14
ሐ) አምላካዊ መልስ/ 14፡15-18
- ዳዊት፡ 1ሳሙ. 30፡1-8
ሀ) የሰዎቹ ዕይታ/30፡6
ለ) የዳዊት ምላሽ/ 30፡7
ሐ) አምላካዊ መልስ/30፡7-8
321_ኢየሱስን ማወቅ ከትንሳኤ በፊት እና ቦኋላ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን (የእሁድ ፋሲካ ቀን ዝግጅት)
321__ኢየሱስን ማወቅ ከትንሳኤ በፊት እና ቦኋላ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን (የእሁድ ፋሲካ ቀን ዝግጅት)
ሉቃስ 24:1-45
...ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።...ሉቃስ 24:15-16
...የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።ኤፌ 1:17
320_በልምድ ሳይሆን በጌታ ቃል ይሁንላችሁ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን
320_በልምድ ሳይሆን በጌታ ቃል ይሁንላችሁ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን (የቅዳሜ ዝግጅት)
ሉቃስ 5 :1-11
...ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው። ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው። ሉቃስ 5 :4-5
319_የመስቀሉ ቃል// ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን
319_የመስቀሉ ቃል// ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን
1ኛ ቆሮ 1:18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። የአርብ(ስቅለት) ቀን አገልግሎት)
የፋሲካ ኮንፈረንስ መሪ ቃል "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል 1ኛ ቆሮ 15:20
318 || እግዚአብሔር ትልቅ ነው! || በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
"እግዚአብሔር ትልቅ ነው ግን ማንንም አይንቅም!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኢዮብ 36፡1-11
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ፊልጵ. 2፡1-12፣ ማቴ. 19፡16-22
317 || ከርግማን በረከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ! || ክፍል 2 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"ከርግማን በርከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ!" በሚል ርዕስ በ2 ክፍል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ሁለተኛው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 30
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማር. 12፡29-30፣ ዮሐ. 14፡15-16፣ 1 ዮሐ. 2፡3-5፣ 1 ሳሙ. 12፡20-21፣ ዮሐ. 14፡4-6፣ ዘዳ. 13፡4፣ ዮሐ. 14፡21-24
316 || ከርግማን በረከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ! || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"ከርግማን በርከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ!" በሚል ርዕስ በ2 ክፍል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 27፣ 28 እና 29
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ገላ. 3፡13-14፣ ዘዳ. 21፡22-23፣ ዘፍ. 12፡3፣ ኢል. 2፡28፣ ሮሜ 6፡14-18፣ 8፡12-14
315 || በክፉው ዓለም ላይ ለእግዚአብሔር መሣሪያ ትሆናላችሁ! || በቄስ ኢዮብ ድንቁ
በማልሚ ሳሌም ኅብረት በቄስ ኢዮብ ድንቁ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፣
መነሻ የየመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኤፌ. 6፡10-20
ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልጉ ነገሮች፦
1) ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን የጦር መሣሪያችን የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ለምን ልዩ ሆነ?
- የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ስለሆነ ነው
- የእግዚአብሔር ቃል ኃይል ስለሆነ ነው
- የእግዚአብሔር ቃል የእምነታችን ምንጭ ስለሆነ ነው
2) ሁለተኛ ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን የጦር መሣሪያችን ጸሎት ነው
3) ሦስተኛ ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን ነገር መጽናት መቻላችን ነው
ለመንፈሳዊ ውጊያ ዝግጅቱ ስንሆን እግዚአብሔር እንዴት ሊጠቀምብን ይችላል?
- ለህዝብ መዳንና ምህረት ማግኘት መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምብናል / ለምሳሌ፦ ዮሴፍና አስቴር ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው
- ያስጨነቀንን በእኛው ሊያዋርድ ሊጠቀምብን ይችላል / ለምሳሌ፦ በሙሴና በፈርዖን መካከል የተፈጠረው ለዚህ ማሳያ ነው
314 || አካልና ብልቶች! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"አካልና ብልቶች!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 12፡12-30
313 || በእውነት መሄድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"በእውነት መሄድ!" በሚል ርዕስ 3ኛው የሐዋሪያው ዮሐንስ መልዕክት ላይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
312 || እኔም አሳርፋችኋለሁ! - ትሕትናን ከክርስቶስ እንማር! || ክፍል 2 || ወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር)
በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል 2።
311 || እኔም አሳርፋችኋለሁ! || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
"እኔም አሳርፋችኋለሁ!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ማቴ. 11፡25-30
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 14፡26-27፣ ሮሜ 5፡1-11፣ ኤፌ. 6፡15፣ ሮሜ 14፡17-20
310 || ክርስቲያናዊ ትሕትና || ክፍል 2 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ
"ክርስቲያናዊ ትሕትና" የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት በወንድም ያቬሎ ናታዬ፣ ክፍል 2።
መነሻ ጥቅሶች፡ 1 ጴጥሮስ 5፡5፣ ፊል. 2፡1-11
ክርስቲያናዊ ትሕትና በክርስቲያን ህይወት የሚገለጥባቸው መንገዶች
1) ለራስ ትክክለኛ ዕይታ መኖር /ሮሜ 12፡3 /
2) ሌሎችን ማስቀደም /ፊል. 2፡3 /
3) ምህረት ማድረግን አለመቸገር / ኤፌ. 4፡32 /
309 || ክርስቲያናዊ ትሕትና || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"ክርስቲያናዊ ትሕትና" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
1) መግቢያ - ትሕትና ምንድን ነው? / መዝ. 86፡1፣ ማቴ. 5፡3/
2) ክርስቲያናዊ ትሕትና / ፊል. 2፡3፣ ኤፌ. 4፡2፣ 1 ጴጥ. 5፡5፣
3) ትሕትና በክርስቶስ ህይወት ምሳሌነት /ማቴ. 11፣ 29፣ ፊል. 2፡1-11/
308 || ለሁሉም ዘመን አለው - ዘመኑ የመገለጥ ነው! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"ለሁሉም ዘመን አለው - ዘመኑ የመገለጥ ነው" - የ2024 ዘመን መለወጫ ዋዜማ መርሃ ግብር ላይ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ መክ. 3፡1-8፣ 1 ነገ. 17፡1-4፣ 1 ነገ. 18፡1-2
31.12.2023 || አዲሱ ስሜ || በወንድም ዮሴፍ አብርሃም የቀረበ ግጥምና መልዕክት
"አዲሱ ስሜ" - የ2024 ዘመን መቀበያ ዋዜማ ላይ በወንድም ዮሴፍ አብርሃም የቀረበ ግጥምና መልዕክት
307 || አሮጌ እርሾና አዲስ ሊጥ! || በፓስተር ዳንኤል ሳቡሬ
"አሮጌ እርሾና አዲስ ሊጥ" - የ2024 ዘመን መለወጫ ዋዜማ መርሃ ግብር ላይ በፓስተር ዳንኤል ሳቡሬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 5፡7
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘጸ. 12፡15፣ ዘጸ. 13፡7፣ ማቴ. 16፡6፣ ማር. 8፡15፣ ገላ. 5፡1-15
306 || የእግዚአብሔር ሥጦታ || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
የእግዚአብሔር ሥጦታ - የኢየሱስ ክርስቶስን ጽንሰትና ውልደት በተመለከተ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 1፡18-25፣ ሉቃ. 1፡26-35፣ ሉቃ. 2፡8-12፣ 21-32፣ 2፡15-20፣ 41-51
305 || ፍለጋውን መከተል! || በእህት ለምለም ጌታቸው
"ፍለጋውን መከተል" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡- መዝ. 25፡4-7፣ ሩት 1፡1-18፣ ማቴ. 25፡1-13፣ ሆሴ. 6፡3፣ ዮሐ. 14፡1-6፣6-7
304 || ኢየሱስን መውደድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"ኢየሱስን መውደድ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን ጥያቄ እየጠየቀ ያገለግላቸው ነበር።
- ማር. 10፡46-51 የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ ተጠየቀ። ቁ. 51 "ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?"
- ዮሐ. 5፡1-8 ለ38 አመታት ሽባ የነበረው ሰው ተጠየቀ። ቁ. 6 "ልትድን ትወዳለህን?"
- ዮሐ. 9፡35-38 ከመወለዱ ጀምሮ ዓይነ ስውር የነበረው ሰውዬ ከቤተ መቅደስ ካስወጡት በኋላ ተጠየቀ። ቁ. 35 "በሰው ልጅ ታምናለህን?"
- ዮሐ. 21፡14-19 ጴጥሮስ ተጠየቀ፡ -
ቁ. 15 "ከእነዚህ አብልጠህ ትወደኛለህን?"
ቁ. 16 "በእውነት ትወደኛለህን?"
ቁ. 17 "ትወደኛለህን?"
ኢየሱስን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው?
- ኢየሱስን መውደድ - ቃሉን መታዘዝ ነው። ዮሐ. 14፡21
- ኢየሱስን መውደድ - ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ መታዘዝ ነው። ዮሐ. 14፡7፣ 12-15/ ሮሜ 8፡15
ጴጥሮስ ለጌታ ጥያቄዎች መልስ ከሰጠ በኋላ በህይወቱ የታዩ ለውጦች፡-
- በጾምና በጸሎት ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር ኅብረት እያደረገ ይተጋ ነበር። ሐዋ. 1
- በበዓለ ሐምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን ይሰብክ ነበር። ሐዋ. 2
- በመንፈስ ተመርቶ ለአህዛብ ወንጌልን መመስከር ተጓዘ። ሐዋ. 10
303 || ቸርነት አደርግለት ዘንድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
በ 2 ሳሙኤል 9 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
302 || እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 9፡1-4፣ 10፡1-2
ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱ ሊያዝን እንደሚችል ተጽፏል፡ -
1) እግዚአብሔር ያዝናል - ዮናስ 4፡11
2) ጌታ ኢየሱስ ያዝናል - ሉቃ.19፡41፣ ዮሐ. 11፡33-34፣ ማር.6፡34
3) መንፈስ ቅዱስ ያዝናል - ኤፌ. 4
ለ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነ ሐዘን
1) በእግዚአብሔር ምህረት ላይ የሚያስቆጣ ነው - ዮናስ 4፡1-3
2) ወደ ኀጢአት የሚወስድ ነው - 2 ሳሙ. 13፡1- 19
3) ተስፋ እንዳይታየን የሚያደርግ ነው - 1 ተሰሎ. 4፡15-18
ሐ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን
1) ሰዎችን ወደ ንስሐ የሚገፋ ነው - ሐዋ. 2፡37-38
2) እግዚአብሔር ሲገስጸን የሚሰማን ሐዘን ነው - 2 ቆሮ. 7፡8-11
3) ሌሎች ችግር ውስጥ ሲሆኑ የሚሰማን ሐዘን ነው - ሮሜ 9፡1-5፣ 10፡1
4) ወደ ጾምና ጸሎት የሚመራ ሐዘን ነው - ነህ. 1፡1-4
301 || የሁላችን አባት - አብርሃም! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
በአባቶች ቀን "የሁላችን አባት - አብርሃም" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ሮሜ 4፡16-17
አብርሃም በእምነት ያደረጋቸው 5 ነገሮች፡ -
1) አብርሃም #በእምነት የታዘዘ ሆነ - ዕብ. 11፡8፣ ዘፍ. 12፡1
2) አብርሃም #በእምነት ተቀመጠ - ዕብ. 11፡9-10፣ ዕብ. 12፡22፣ 1 ጴጥ. 2፡11፣ ፊል. 3፡20
3) አብርሃም #በእምነት ተስፋ አደረገ - ሮሜ 4፡18፣ ዕብ. 11፡11፣ ዘፍ. 15
4) አብርሃም #በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ - ሮሜ 4፡19
5) አብርሃም #በእምነቱ በረታ/ጸና እንጂ አተጠራጠረም - ሮሜ 4፡20
> እምነቱም ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት - 4፡22-23
300 || ጌታ ሊያድ'ሰን ይፈልጋል! || በወንድም አብርሃም ፈንተ
"ጌታ ሊያድ'ሰን ይፈልጋል!" በሚል ርዕስ በወንድም አብርሃም ፈንተ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
1) እግዚአብሔር እንዲያድሰን፣ ትሑት መሆን ከእኛ ይጠበቃል። ኢሳ. 66፡2፣ መዝ. 51፡12፣
2) እግዚአብሔር እኛን የሚያድስበት ዓላማ / ለእውነተኛው አምላክ ምስክሮች እንድንሆን ነው።
3) የእግዚአብሔር ተልዕኮ ለእኛ
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ሳሙኤል 30፡1-> ፣ ዕብ. 3፡13፣ 1 ጴጥ. 5፡6፣ ዘሌ. 18፡15፣ ፊል. 2፡5-11፣ ሮሜ 1፡16፣ 1 ዮሐ. 1፡1፣
299 || ጌታ በርግጥ ይመጣል! || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"ጌታ በርግጥ ይመጣል!" በሚል ርዕስ የቀረበ የሚልክያስ ትንቢት መጽሐፍ ዳሰሳ።
298 || እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል! || በፓስተር አለማየሁ ሙልጌታ
"እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!" በሚል ርዕስ በፓስተር አለማየሁ ሙልጌታ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ርዕስ: እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!
1) እግዚአብሔር ቀዳሚው አጀንዳው ሰዎችን ማዳን ነው/ መሳ. 3፣ 10፣ ኢሳ. 9፡6-7፣ ማቴ. 1፡20-21፣ ቲቶ 2፡10-11፣ ሮሜ 1፡16-17
2) ሰዎች ነፍሳቸው እንድትድንና ከክፋት እንዲጠበቁ እግዚአብሔር ይፈልጋል / ዮሐ. 17፡15
3) እግዚአብሔር በእኛ በኩል ሰዎችን ማዳን ይፈጋል
1) የዮሴፍ ታሪክ
2) የሶሪያዊው ንዕማን አገልጋይ ታሪክ
3) የአስቴር ታሪክ
297 || ቃሉ ያሸንፋል! || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
"ቃሉ ያሸንፋል!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ዮሐ. 1፡1-13፣ 1 ዮሐ. 1፡1-5፣ 2፡1-4፣ 3፡1-4፣ ራዕ. 22፡12-21
296 || ቅዱስ ጥበብ || በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር)
"ቅዱስ ጥበብ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ምሳሌ 1፡7፣ 1 ጴጥሮስ 1፡13-17፣ ሉቃስ 2፡32፣ ሮሜ 3፡11-12፣ 1 ዮሐ. 4፡13-21
295 || ታምራትን ለማየት ወደፊት ቀጥል! || በፓስተር ሰሎሞን አምዴ
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "ታምራትን ለማየት ወደፊት ቀጥል!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዘጸዐት 14፡15-16
ሌሎች ክፍሎች፡ ዕብ. 10፡35-38፣ 1 ቆሮ. 11፡17
294 || ሙሽራውን ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ! || በእህት ሊድያ ተስፋዬ
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "ሙሽራውን ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ!" በሚል ርዕስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ማቴ. 25፡1-13
293 || እግዚአብሔርን ህዝቡን መባረክ ይፈልጋል! || በፓስተር ሰሎሞን አምዴ
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "እግዚአብሔር ህዝቡን መባረክ ይፈልጋል!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ትንቢተ ሐጌ ምዕራፍ 1 እና 2
292 || ምን ተደርገሃል/ሻል? || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"ምን ተደርገሃል/ሻል?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ቃል፡ ዮሐ. 1፡19-23
291 || የጌታን መንገድ መከተል እንዲህ ይጀምራል! || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
የትምህርቱ ማጠቃለያ - መነሻ ክፍል ሉቃስ 9፡23-27
290 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 16 - የመጨረሻው ክፍል || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 15፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
4) የጸሎቱ መደምደሚያ
1) ዘላለማዊ መንግሥት የእግዚአብሔር ነው
2) ዘላለማዊ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
3) ዘላለማዊ ክብር የእግዚአብሔር ነው
289 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 15 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 15፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
3) ምድራዊ ህይወታችንን የሚመለከተው የጸሎቱ ክፍል
ሀ) ዕለት በዕለት ስለሚያስፈልጉን ነገሮች መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡11፣ ማቴ. 6፡25፣ 31-32፣ ፊልጵስዩስ 4፡6፣
ለ) በሌሎች ሰዎችና በእኛ መካከል ስለሚኖረን ግንኙነት መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡12፣ ሉቃስ 11፡4፣ 1 ዮሐንስ 4፡8፣
ሐ) እግዚአብሔር ከፈተናና ከክፉው እንዲጠብቀን መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡13ሀ፣ ማቴ. 26፡41፣ ማቴ. 13፡37-39፣ 1 ጴጥሮስ 5፡5-8፣ 1 ተሰሎ. 3፡3
288 || የሐዋሪያው የጳውሎስ ጸሎት ለፊልጵስዩስ አማኞች || በፓስተር ሳምሶን ስምዖን
በማልሚ ሳሌም ኅብረት በነበረው ኮንፍራንስ ላይ በፓስተር ሳምሶን ስምዖን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ ፊልጵ. 1፡8-11
287 || ምን ይታይሃል/ሻል/ችኋል? || በፓስተር ሚልክያስ ደገፉ
"ምን ይታይሃል/ይታይሻል/ይታያችኋል?'' በሚል ርዕስ በፓስተር ሚልክያስ ደገፉ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡- ማርቆስ 8፡22-25፣ ኤርሚያስ 1፡11-12
286b || የዝማሬ አምልኮ፣ የማስታወቂያና የጸሎት ጊዜ በአንድነት
በአምልኮ ሥፍራው ላልነበሩ ሲባል በዚህ ገጽ በኩል የቀረበ፣ የዝማሬ አምልኮ፣ የማስታወቂያና የጸሎት ጊዜ በአንድነት
286 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 14 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 14፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
2) የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ የሚያተኩረው የጸሎት ክፍል (ማቴ. 6፡ 9ሐ - 10ለ)
ሀ) የእግዚአብሔርን ስም መቀደስ / ማቴ. 6፡9ሐ፣ ዘሌ. 11፡44፣ ኢሳያስ 8፡13/
ለ) የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትመጣ መለመን /ማቴ. 6፡10ሀ፣ ሮሜ 14፡17፣ ማቴ. 5፡6፣ ማቴ. 6፡33/
ሐ) የእግዚአብሔር ፈቃድ በምድር እንዲሆን መለመን /ማቴ. 6፡10ለ፣ ሮሜ 8፡14፣ ሮሜ 12፡2
285 || የፍቅር ዕዳ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"የፍቅር ዕዳ አለብን!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ሮሜ 13፡8
መግቢያ፡ ቆላ. 2፡14፣ ገላ. 3፡13፣ 1 ቆሮ. 6፡19-20
በክርስቶስ ነጻ የወጣን 3 ዓይነት ዕዳ አለብን፡ -
1) የወንጌል ዕዳ አለብን ሮሜ 1፡14-15፣ ሐዋ. 9፡1-19
2) ለጌታ ተለይተን በቅድስና ህይወት የመኖር ዕዳ አለብን ሮሜ 8፡12-13
3) ሌሎችን የመውደድ ዕዳ አለብን ሮሜ 13፡8፣ ሮሜ 15፡24-27
ማቴ. 18፡21-35
284 || ክቡር የሆነው እምነትና ተስፋችን! || በእህት ለምለም ጌታቸው
"ክቡር የሆነው እምነትና ተስፋችን!" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ /2 ጴጥሮስ 1፡1-11/
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ /1 ጴጥሮስ ከምዕራፍ 1-5፣ ዮሐ. 21፡15-22፣ ኤርሚያስ 32፡17-19፣ ምሳሌ 2፡6፣ ገላቲያ 5፡22-23/
283 || የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ!/እግዚአብሔርን ፍራ! || ክፍል 2 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"እግዚአብሔርን ፍራ/የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። ክፍል 2
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ፡ መክብብ 12፡1 3-14
እግዚአብሔርን ስለመፍራት 10 ነጥቦች፡ -
1) እግዚአብሔርን ፍራ የሚለው ትዕዛዝ ለእግዚአብሔር ህዝብ የተሰጠ ነው /1 ጴጥሮስ 2፡17፣ ዘዳግም 6፡13፣ ዘዳግም 10፡20/
2) እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው /ምሳሌ 1፡7፣ መዝሙር 111፡10፣ 1 ቆሮንቶስ 1፡20-25/
3) እግዚአብሔርን መፍራት የምንማረውና የምናድግበት ነገር ነው /ዘዳግም 17፡19-20፣ ዘዳግም 31፡13/
4) እግዚአብሔርን መፍራት የሚታይ ነገር ነው /ዘፍጥረት 20፡9-11/
5) እግዚአብሔርን መፍራት ከኃጢአት መራቅ ነው /ኢዮብ 28፡28/
6) እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል /ምሳሌ 8፡13/
7) እግዚአብሔርን መፍራት በኃጢአተኛ አይቀናም /መዝሙር 73፡1-28፣ ምሳሌ 23፡17-18/
8) እግዚአብሔርን መፍራት የእግዚአብሔርን ቃል ያስቀድማል /ምሳሌ 1፡29-31/
9) እግዚአብሔርን መፍራት በደልና በሰው ፊት ማድላት የለውም /2ዜና 19፡6-9/
10) እግዚአብሔርን መፍራት ከህይወት ሊጠፋ ይችላል /ኢዮብ 15፡4/
282 || የነገሩን ፍጻሜ እንስማ! || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን
"የነገሩን ፍጻሜ እንስማ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ መክብብ 12፡1-12
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች / 1 ነገሥት 11፡1-6፣ ሮሜ 10፡17፣ ዳንኤል 5፡1-31 /