የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
By Yetena Weg ®
A production of Yetena Weg Health Promotion team.
Our podcasts focus on general medical care, mental health, and health policy issues.
We invite expert guests on each topic to bring you quality, evidence-based content.
Yetena Weg is a legally registered nonprofit, based in the USA. It is run by an all-volunteer team of health care professionals.
ይህን ፕሮግራም በቤታችሁ ሆናችሁ ፣ መኪናም እየነዳችሁም ፣ እንቅስቃሴም በምታረጉበት ሰአት ወይም ባላችሁ ማንኛውም ትርፍ ግዜ
እንድታዳምጡት አስበን ያዘጋጀነው ነው። ያሉዋችሁን ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች በተለያዩ የማህበራዊ መድረኮች በተለይም በትዊተር እና ፌስ ቡክ ብታደርሱን ፣ በቀጣይ ፕሮግራሞቻችን ላይ ለመመለስ እንሞክራለን ።
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ® Mar 18, 2020
የልብ በሽታ በሴቶች/ Heart Disease in Women
🫀የልብ በሽታ በሴቶች
በዚህ ፖድካስት የጤና ወግ ከሮሀ ሜዲካል ካምፖስ ጋር በመተባበር የልብ በሽታ በሴቶች በሚል ርዕስ ስለተለያዩ
👉የልብ በሽታ መንስኤዎች
👉ምልክቶች
👉በሴቶች ላይ የልብ በሽታ እንዴት እንደሚለይ እና
👉የሕክምና አማራጮች እንወያያለን።
ከእንግዶቻችን
✨ዶ/ር ብስራት ደመቀ (የውስጥ ደዌ እና የልብ ሐኪም እና ተባባሪ ፕሮፌሰር ) እና
✨ዶ/ር እዮኤል ውህብ (የውስጥ ደዌ ሐኪም) ከሮሀ ሜዲካል ካምፖስ ጋር ይከታተሉን።
In this podcast, we discuss Heart Disease in Women, the various risk factors, different clinical presentations and the treatment options with our guests Dr. Bisrat Demeke (Internist and Cardiologist) and Dr. Eyoel Wuhib (Internist).
የስኳር በሽታ እና ከልክ ያለፈ ውፍረት/ Diabetes and Obesity
በዚህ ፖድካስት ስለ ስኳር በሽታ አጋላጮች፣ ምልክቶቹ እና ስለ ሕክምናው ከእንግዶቻችን ከዶ/ር ቃልኪዳን አላቸው (የስኳርና የኢንዶክራይን ህመሞች ስፔሻሊስት) እና ከትርሲት ደምሰው (የስነ ምግብ ባለሙያ) ጋር ተወያይተናል።
In this podcast, we discuss about diabetes, risk factors, clinical presentation and medical care with our guests Dr. Kalkidan Alachew (Endocrinologist) and Tirsit Demissew (Dietician).
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው "ሲስተም ቦትልኔክ ፎከስድ ሪፎርም (SBFR)" ፕሮግራም ስንል ምን ማለታችን ነው?
What is "System Bottlenecks Focused Reform (SBFR)” program in Ethiopia?
Managing Healthcare at low cost with limited resources
👉🏾Have you ever heard about the “system bottlenecks focused reform (SBFR)” program in Ethiopia?
👉🏾ስለ "ሲስተም ቦትልኔክ ፎከስድ ሪፎርም (SBFR)" ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሰምተው ያውቃሉ? (ስርዓተ ማነቆዎች ተኮር ሪፎርም )
▶️Join us for a game-changing discussion on SBFR - the newly designed pilot project aimed at improving hospital service delivery and enhancing patient outcomes.
▶️የሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የታካሚውን ውጤት ለማሻሻል የታለመው አዲስ የተነደፈው የሙከራ ፕሮጀክት (SBFR) ላይ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉን።
▶️የSBFR ፕሮግራም እንዴት እንደሚተገበር እና እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ውይይቱን እንዳያመልጥዎ።
ትኩረታችንን ለሚጥል በሽታ
ትኩረታችንን ለሚጥል በሽታ
ስለየሚጥል በሽታ ምን ያህል ያውቃሉ?
👉🏾 የሚጥል በሽታ ስንል ምን ማለት ነው?
👉🏾 ምልክቶቹስ ምንድናቸው?
👉🏾 መንስኤዎቹስ ምንድናቸው?
👉🏾 ህክምናስ አለው? የተጎዱትን እንዴት መደገፍ እንችላለን?
ከነርቭ ሐኪሙ ዶ/ር ደረጄ መልካ ጋር ያዳምጡ
ስለ Monkey pox (የጦጣ ፈንጣጣ) አንዳንድ እውነታዎች !! ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ
ስለ Monkey pox (የጦጣ ፈንጣጣ) አንዳንድ እውነታዎች !!
Dr. Tinsae Alemayehu
ስለ ኦቲዝም ስፔክትረም እንወያይ
ኦቲዝም ስንል ምን ማለት ነው?
አጠቃላይ የአእምሮ ጤና ጉዞ በኢትዮጵያ
ስለ የአእምሮ ጤና ጉዞ በኢትዮጵያ እንወያይ
የህክምና መረጃ ሚስጥራዊነት, ፈቃድ አሰጣጥና የሀኪም ታካሚ ግንኙነት/Confidentiality, Consent and Patient-Physician Relation
ሞትና መሪር ሀዘን/ Grief and Loss
የአካል ጉዳተኝነት እና የህክምና ትምህርት ተደራሽነት/ተካታችነት በኢትዮጵያ- Accessibility, Inclusiveness and Disability Rights in Ethiopian Medical Schools
በዚህ ፖድካስት አካል ጉዳተኞች በትምህርት ሥርዓቱ በተለይም በህክምና ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን የመዋቅር እና የአመለካከት ችግሮች በሚመለከት ከእንግዶቻችን ፕሮፌሰር አበበ በቀለ እና አቶ ዳኛቸው ዋኬን ጋር አስደናቂ ውይይት አድርገናል።
In this podcast, we had a fascinating discussion with our guests Professor Abebe Bekele and Ato Dagnachew B. Wakene concerning the structural and attitudinal obstacles that people with disability face in the educational system and in particular in our medical schools.
የጤና ወጪና እና የጤና መድህን በኢትዮጵያ/ Health care financing and Health Insurance in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት ስለ ጤና መድህን አስፈላጊነት እና በሀገሪቱ የጤና መድህን ስርዓትን ለማቋቋም ስለሚደረገው ጥረት ተወያይተናል። እንግዶቻችን ፍሬህይወት አበበ፣ አለማየሁ ካብተይመር፣ ህሊና ከበረ እና ዶ/ር ቅድስት መላኩ ነበሩ።
In this podcast, we discussed about the need of health insurance and the efforts to institute health insurance systems in the country. Our guests were Frehiwot Abebe, Alemayehu Kabtyimer, Helina Kebere and Dr. Kidist Melaku.
በሕግና በአዕምሮ ሕመም መካከል ያለው መስተጋብር/ The Intersection between Mental Health and the law
በዚህ ፖድካስት በሕግና በአዕምሮ ሕመም መካከል ስላለው መስተጋብር በኢትዮጵያ ብቸኛ ፎሬንዚክ ሳይኪያትሪስት ከሆነው ከዶ/ር አስናቀ ልመንህ ጋር ተወያይተናል።
In this podcast, we discussed about the interaction between law and mental illness with the one and only Forensic Psychiatrist in Ethiopia, Dr. Asnake Limenih.
የህክምና ትምህርት ጥራት በኢትዮጵያ/ Quality of Medical Education in Ethiopia
እንግዶቻችን
1. አሰግድ ሳሙኤል ጤና ሚኒስትር (የሰው ሃይል ለጤና የልማት ዳይሬክቶሬት)
2. አቢይ ደባይ ኢ.ት.ስ.ባ (የእውቅና ዳይሬክተር)
3. ዶ/ር እልልታ ነጋ፣ ጤና ሚኒስትር (የሰው ሃይል ለጤና የልማት ዳይሬክቶሬት)
4. ሳብሪና ዘለቀ (የህክምና ተማሪዎች ማህበር)
5. ዶ/ር ፀደቀ አሳምነው (የአይን ሐኪም ስፔሻሊስት፣ የቫትሮ-ሬቲናል ንዑስ ስፔሻሊስት፣ የህክምና አስተማሪ)
የአንቲባዮቲክ (ፀረ ተውኃሲያን መድኃኒቶች) ሽያጭ ደንብና ቁጥጥር በኢትዮጵያ/ Regulation of Antibiotic Sale in Ethiopia
In this podcast, we discussed about the structure of the EFDA, the overall regulatory activities including the challenged and the way forward. Our guests were Asnakech Alemu (EFDA), Getachew Alemkere (AAU School of Pharmacy) , Dr. Eskedar Ferdu (AAU, Infectious Disease Unit) and Million Tirfe (EFDA).
ኢ.ም.መ.ቁ.ባ/EFDA: የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን/ Ethiopian Food and Drug Authority
ሲጋራ እና ሺሻ/ Smoking Cigarettes and Hookah
የወሳኝ መድሀኒቶች አቅርቦት በኢትዮጵያ/ Access to Essential Medicine in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት ስለ ወቅታዊው የመድሃኒት አቅርቦት ሁኔታ ተነጋግረናል። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ዘላቂ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ተግዳሮቶችን እና መፍትሄዎችን እናነሳለን። እንግዶቻችን ዶ/ር ሎኮ አብርሀም (የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ባለስልጣን የቀድሞ ዳይሬክተር) አማኑኤል ዝናረ (የግል ዘርፍ) እና ሰለሞን አብደላ (ጤና ሚኒስትር) ናቸው።
In this podcast, we discuss about the current state of medication supply in the country. We also raise the challenges that are currently hampering sustainable supply and the possible solutions. Our guests are Dr. Loko Abraham (former Director of EPSA), Amanuel Zinare (Private Sector) and Solomon Abdela (FMOH/PMED).
የጤና መረጃ ጥራት በኢትዮጵያ/ Quality of Health Data in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት የጤና መረጃ በጤና ስርዓታችን ውስጥ ስላለው ጠቀሜታ፣0 ያሉትን ተግዳሮቶች፣ እድሎችን እና ወቅታዊ ጥረቶችን እናነሳለን። ተወያዮቻችን ናኦድ ወንድይራድ፣ ዶ/ር ደሳለኝ በቀለ፣ ሰናይት ቢተው እና ዶ/ር የቆየሰው ወርቁ ናቸው።
In this podcast, we discuss about the importance of health data in our health system and raise the challenges, opportunities and current efforts. Our panelists are Naod Wondirad, Dr. Desalegn Bekele, Senait Bitew and Dr. Yekoyesew Worku
ከድባቴ ጋር መኖር/ Living with Depression
በዚህ ፖድካስት ከያፌት ከፈለኝ፣ ከዶ/ር የፍሬዘር ገዛኸኝ፣ ከዶ/ር ማጂ ኃ/ማርያም እና ከዶ/ር ሄርሞን አማረ ጋር ስለ ድባቴ፣ የመቋቋሚያ ክህሎቶች እና የህክምና አገልግሎት እንወያያለን።
In this podcast, we discuss about Depression, coping skills and medical care with Yafet Kefelegn, Dr. Yefrezer Gezahegn, Dr. Maji H/Mariam and Dr. Hermon Amare.
የኩላሊት ህክምና በኢትዮጲያ ምን ይመስላል? Kidney disease care, Dialysis and Kidney transplant service in Ethiopia
በዚህ ፖድካስታችን የኩላሊት ህመም ስፔሺያሊስት ከሆኑት ዶ/ር ቤዛዬ አበበ ፣ ዶ/ር ሰይፈሚካኤል ጌታቸው እና ዶ/ር ፍፁም ጥላሁን ጋር ስለ ኩላሊት ጤና አጠባበቅ፣ ስለ ኩላሊት መድከም፣ ስለ ዳያሊሲስ እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ውይይት አድርገናል።
In this podcast, we discussed kidney health, kidney failure, dialysis and kidney transplantation services in Ethiopia with our guest nephrologists Dr. Bezaye Abebe, Dr. Seyfemichael Getachew and Dr. Fitsum Tilahun.
የጤና ባለሙያዎቻችን መታከት፣ ለምን?/ Burnout among our Healthcare Professionals
በዚህ ፖድካስት ስለ የጤና ባለሙያዎቻችን መታከት ከዶክተር መድህን ሰላሙ ጋር ተወያይተናል። ዶ/ር መድህን በዚህ ርዕስ ላይ ሰፊ ጥናት አድርገዋል። የጤና ሚኒስቴር ኃላፊዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አቅርበናል።
In this podcast, we discussed about burnout among our health care professionals with Dr.Medhin Selamu on our Yetena Weg Club House session. Dr.Medhin has done an extensive research on this topic . We also featured officials from the Minstry of Health and other stakeholders.
የስትሮክ ህመም ምንድነው? ህክምናውስ? ከዶ/ር መሀሪ ጋር / Stroke - Types, Diagnosis and management with Dr.Mehari
ስለ ስትሮክ ህመም ፣ ምርመራ እና ህክምና በጤና ወግ ክለብ ሀውስ ከዶ/ር መሀሪ ገብረየኋንስ ጋር ያደረግነውን ውይይት ነው። ሰለ ስትሮክ ህመም አይነቶች፣ በምን ምክንያት እንደሚከሰት ፣እንዴት እንደሚታከም እና እንዴት መከላከል እንደምንችል ተወያይተናል። ዶ/ር መሀሪ በ University of Texas South Western የ ኒውሮሎጂ እና ስትሮክ ሰብ ስፔሺያሊስት ናቸው። በሀገራችንም ኢትዮጲይ ያሉ ባለሙያዎች በውይይቱ ተካፋይ ነበሩ። በሀገራችን ያለውን የስትሮክ ህክምና ደረጃ ያስረዱናል።
This is the conversation with Dr. Mehari Gebreywanes, we talked about definition of stroke, its diagnosis and treatment. We also discussed the types of stroke, and how to prevent it. Dr. Mehari is a neurology and stroke specialist at the University of Texas Southwestern. Experts from our country, Ethiopia, participated in the discussion. They explain the level of stroke treatment in our country.
በጦርነት ወቅት ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮች / The Impact of War/Conflict on Mental Health, focus in Ethiopia
ከጦርነትና ግጭቶች ጋር ተያይዞ ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮችና ችግሩን ለመፍታት በኢትዮጵያ ምን እንደታሰበ ከአእምሮ ጤና ባለሞያ እና ከጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት
A discussion with mental health experts and Ministry of Health officials about mental health problems that arise in connection with war and conflict and what is being planned in Ethiopia to solve the problem
ስለ ጨጓራ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች። ቆይታ ከ ዶ/ር ኤርምያስ ጋር።
What you should know about Rheumatoid arthritis ? የ ሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው?
What you should know about Rheumatoid arthritis ?
የ ሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው?
ለህመሙ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድናቸው ?
ምልክቶቹ ምንድናቸው ?
ምርመራዎቹ ምንድናቸው ?
ሕክምናው ምን ይመስላል ?
በዚህ ፖድካስት በዝርዝር እንወያያለን
Updates on COVID-19 Infection and Vaccinations. የ ኮቪድ 19 በሽታ እና ክትባቶቹ ላይ ማወቅ የሚገባችሁ መረጃዎች
የተለያዩ አይነት የኮቪድ ዝርያዎች (Variants ) አሉ ? ልዩነታቸው ምንድነው ? በክትባቱ ላይ የሚያመጡት ተፅእኖ ምንድነው?
በኮቪድ የተያዘ ሰው ክትባቱን መውሰድ ይችላል ወይ? መቼ ( በምንያህል ጊዜ ውስጥ ?)
በ ዓለም ላይ የሚታየው ፍትሓዊ ያልሆነ የክትባት ስርጭት የሚፈጥረው ችግር ምንድነው?
እና ከናንተ የደረሱንን ጥያቄዎች መልሰናል ።
ስለ ቲቢ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች
!
መተላለፊያው ፣ምርመራው ፣ሕክምናው ምን ይመስላል ?
በ ዓለም ላይ ሞትን ከሚያስከትሉ ታላላፊ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥር 1 ገዳይ በሽታ ነው ።
ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ የቲቢ ታማሚ እና በቲቢ ምክንያት ሰዎች ከሚሞቱባቸው 30 አገራት አንዷ ነች።
በዚህ ፖድካስታችን ስለ ቲቢ በሽታ እንወያያለን በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው እንዴት ይተላለፋል?
የበሽታው ዋና ምልክቶች ምንድናቸው?
የቲቢ በሽታ በምን አይነት ምርመራ ይረጋገጣል?
ሕክምናው ምን ይመስላል ?
ሕክምናው ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
ቤት ውስጥ የታመመ ሰው ካለ ምን አይነት ጥንቃቄ ነው ማድረግ ያለብን ?
እነዚህን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን እንመልሳለን።
What we know so far about COVID 19 Vaccines? ተገኙ በተባሉት ኮቪድ 19 ክትባቶች ዙሪያ ቆይታ ከዶ/ር በለጠ ጋር
ጫት በጤናችን ላይ ምን ተፅዕኖ አለው? በኢትዮጲይ እና በአከባቢው ሀገራት የተሰሩ ጥናቶችን እንመለከታለን።
ትምህርት ቤቶችን መቼ እንክፈት ? የልጆቻችንን፣ የመምህራንን እና የወላጆችን ደህንነት እንዴት እንጠብቃለን? ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ ይመልሳሉ።
የስትሮክ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይታከማል?/እንዴትስ መከላከል ይቻላል?
• ስትሮክ ምንድን ነው?
• ለስትሮክ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምንድናቸዉ?
• በስትሮክ የተያዙ ሰዎች ሊያሳያቸዉ የሚችሉ ምልክቶች ምንድናቸዉ?
• አንድ ሰው ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማወቅ ይችላል?
• አንድ ሰዉ ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?
• ስትሮክ እንዴት ሊታከም ይችላል?
• ስትሮክ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይችላል?
• ከስትሮክ ቡሃላ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች ምንድናቸዉ?
• የስትሮክ የመልሶ ማቋቋም (Stroke Rehab)
• ከስትሮክ በኋላ ሙሉ በሙሉ የማገገም እድሎች በምን ይወሰናሉ?
• በሌላ ስትሮክ በድጋሚ ላለመያዝ ምን ማድረግ አለብኝ?
ስለ አስም በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች
?
የደም ማነስ በሽታ ምንድነው
?
ከልክ ያለፈ ውፍረት (Obesity) - ምክንያቶቹ፣ በጤና ላይ የሚያስከትለው ችግሮች እና እንዴት ከልክ ያለፈ ውፍረትን መቀነስ እንደምንችል እንነጋገራለን።
Health Risks of Smoking. ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ?
በዚህ ፖድካስታችን ስለ ትምባሆ (ሲጋራ ) ማጨስ ጉዳቶች በሰፊው እንወያያለን ።
የ ምናነሳቸው ሃሳቦች 📍
*የትንባሆ አይነቶች ምንድን ናቸው? አጠቃቀማቸውስ? 📍
* አንዱ ከሌላው በሚፈጥሩት ጉዳት ይለያያሉ ወይ?
*📍 መደበኛ ሲጋራ ፣ ሺሻ ወይም ሁካ እና የ ኤለክትሮንክ ሲጋራ ያላቸውን ልዩነት እናያለን
📍*ሺሻ /ሁካህ ከ ተለመደው ሲጋራ በባሰ መልኩ እንዴት የጤና ችግር እንደሚያመጣ እንነጋገራለን 📍
*በ እርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ሴቶች ወይም ለሲጋራ ጭስ በተዘዋዋሪ የሚጋለጡ እናቶች በራሳቸው እና በሚወልዱት ልጅ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አንስተን እንነጋገራለን
📍ከሁለተኛ እጅ የተጎዳኘ ጭስ መጋለጥ የሚፈጥራቸው የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው?
📍አጫሾች ማጨስ ቢያቆሙ ምን የጤና ጥቅሞች ሊያገኙ ይችላሉ?
📍ከዚያ በኋላ ሲጋራ ማቆም ጥቅም የለውም የሚባልበት አድሜ አለ አንዴ?
📍ለአጫሾች ለምን ማቆም ይከብዳል?
ለማቆም ምን ማረግ አለባቸው?
በኮቪድ የተያዘ ሰው አራሱን ቤት ውስጥ ማስታመም ቢኖርበት ወይም በኮቪድ የተያዘን ሰው ማስታመም ቢኖርብን ልናውቅ የሚገቡን የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው?
2 ከአሜሪካ ተሞክሮ ምን አንማራለን
3 አራሳችንን ቤት ዉስጥ አግለን ስንከባከብ መከተል ያሉብን ነገሮች ምንድን ናቸው?
4 ድንገተኛና አደገኛ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
5 ቤተሰብ ስንከባከብ መከተል ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው?
6 ቀብርንስ በተመለከተ ምን አዲስ ነገር አለ? ምን አይነት መከላከያዎችን መከተል አለብን?
7 አካል ጉዳተኞች አንዴት የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ? ምን ማድረግ ይገባናል?
8 አርጉዝ አናቶችን በተመለከተስ? ጡት ማትባትስ ? ሁሉንም አንስተን ተወያይተናል።
ስለ ኩላሊት ህመም ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? ቆይታ ከ ዶ/ር ፍጹም ጥላሁን (የኩላሊት ህክምና ስፔሺያሊስት ) የጤና ወግ አዘጋጅ።
Let's Talk about Suicide. በዚህ የጤና ወጋችን ሰው ለምን ራሱን ወደ መግደል (ራስን ማጥፋት )/ይሄዳል ላይ እንወያያለን።
Blood donations during #COVID19 በኮቪድ 19 ወቅት ደም ስንለግስ ማወቅ ያለብን ነገሮች።
COVID 19 -Current Strategies and Plans Ahead. የ ኮቪድ 19 የፖሊስ አማራጮችና ቀጣይ አርምጃዎች።
Also discussed why lockdown may not be a good option for Ethiopia , but working on Moderate social distancing with other steps excuted on a longer period can help curb the spread of disease and may give a cushion to economic fallout.
የ ኮቪድ 19 የፖሊስ አማራጮችና ቀጣይ አርምጃዎች። ከዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ የጤና ኢኮኖሚስት (MD, MPH ) እና ከዶክተር በለጠ (MD, Phd) በ አሜሪካ የጤና ምርምር ተቁዋም የ ቫይረሶች ተመራማሪ ጋር
ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ተወያይተናል።
1. በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ፣ የወቅቱ ስርጭት መጠን ፣ የኢትዮጵያ ትንበያ ፣በመካሄድ ላይ ያለው የመንግስት ምላሽ
2 ቫይረሱ እንዴት እንደሚሰራጭ ማወቅ በተለይም አዳዲስ መረጃዎች እንዴት ፖሊሲ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ
3 በኢትዮጵያ ለተከሰተው ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የህብረተሰባችን ፣ የወረዳ እና የሆስፒታል ደረጃዎች የጤና ስርዓታችንን ማደራጀት ያለበት እንዴት ነው?
4 መንግስት ፈጠራን በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ አዳዲስ አሰራሮችን በፍጥነት በማስተካከል ምን ያህል ደረጃ አያዋለ ነው ?
5 ሁሉን ነገሮች መዝጋት ? ለምን ? እና ለምን አይሆንም? ኢትዮጵያስ ይህን ማረግ ይኖርባታል?
እና ሌሎችንም ነገሮች ተወያይተናል። እባካችሁ አዳምጡት።
Psychology of Pandemics. በዚህ ወጋችን የአእምሮ ጤናን በወረርሽኝ ወቅት እንዴት እንደምንጠብቅ እንወያያለን።
Care of Chronic diseases in a Pandemic. በ ኮቪድ 19 ምክንያት ከቤት መውጣት ያልቻሉ ሰዎች ህክምና እንዴት ማግኘት ይችላሉ?
እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞች በሚነሱበት ጊዜ ቀጥተኛ ጉዳታቸው ብዙ ነው ። በ ሚድል ኤጅስ ዘመን (Middle Ages ) የተነሳው ጥቁር ሞት (Black Death ) ከ 30-50 ሚልየን ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። በቅርብ ደግሞ የ HIV pandemic ምክንያት ከ1981 ጀምሮ ከ35 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞተዋል።
የኮሮና ቫይረስም አሁን በአለም ላይ ከአንድ ሚልየን በላይ ሰዎችን ይዟል። እና ከ 50000 በላይ ሰዎች ደግሞ
ለሞት ተዳርገዋል። የኢኮኖሚ ጉዳቱ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው።
አሁን ማንሳት የፈለግነው ደግሞ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንዴት ሌሎች ዘላቂ ህመም ያላቸው ሰዎች በ ክትትል ማነስ ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው። በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰዎች በ ተላልፊ በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ፣ በ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች መጣበብ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መዋላቸው የ አነዚህን ህመምተኞች ሕክምና በጣም ይጎዳዋል።
ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300 ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል።
ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ህመም ያላቸው ሰዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸት አለበት። የተለያዩ የህክምና ተቋማት ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ምን እያደረጉ እንደሆነ በዚች አጭር የጤና ወግ ውይይታችን እናያለን ።
በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሌላ ዘላቂ የሆነ የጤና ያለባቸው ሰዎች ሕክምና እንዳይቃረጥ መስራት አለብን
Herd Immunity ምንድነው?
Herd Immunity ማለት በአንድ ማህበረሰብ ያሉ ሰዎች ውስጥ ለ አንድ ተላላፊ በሽታ ምን ያህሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ነው የሚነግረን። ሰዎች ይሄን የመከላከል አቅም ወይ ታመው ከበሽታው ሲያገግሙ ያገኙታል ወይም በ ሕብረተሰብ ጤና የሚመረጠው ደግም ማህበረሰብ አቀፍ በሆነ የክትባት ዘመቻ ሁልኑም ወይም አብዛኛውን ሕብረተሰብ ማዳረስ ሲቻል ነው።
Herd Effect የምንለው ደግሞ በ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ የ Herd Immunity በመኖሩ የ አንድ በሽታ ከ አንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ እድሉ ሲቀንስ ነው። ምን ያህሉ ሰው ለ አንድ በሽታ የመከላከል አቅም ሲኖረው ነው ይሄን Herd Effect የምናየው የሚለው የሚወሰነው በሽታው ምን ያህል ተላላፊ ነው በሚለው ነው።